Assosa University

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት በሦስት አጀንዳዎች ላይ ውሳኔዎችን አሳለፈ

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት የሬሜድያል ተማሪዎች ቅበላ፣ የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ውጤት ማፅደቅ እና የዩኒቨርሲቲው መሪ ቃል አመራረጥ ዙሪያ ተወያይቶ ዉሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
በስብሰባው የ2017 ዓ/ም የሬሜዲያል ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥር 22- 23 2017 ዓ/ም እንዲሆን ወስኗል፡፡በተጨማሪም በሁለተኛ ዲግሪ መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎችን ውጤት አጽድቋል፡፡
በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲውን መሪ ቃል በተመለከተ ለዩኒቨርሲቲው እና ለአካባቢው ማህበረሰብ ለውድድር ቀርቦ ምርጫ እንዲካሄድ ሴኔቱ ወስኖ ስብሰባው ተጠናቋል።
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *