Assosa University

የዩኒቨርሲቲዉ አመራሮች ቁልፍ ዉጤት አመላካች ዉል ስምምነት ተፈራረሙ

ዩዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ከማል አብዱራሂም ከዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዝዳንቶች ጋር የቁልፍ ዉጤት አመላካች ዉል ተፈራመዋል። በተመሳሳይ የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዝዳንቶች ከሚመሯቸዉ የሥራ አስፈፃሚዎች ፣ኮሌጅ ዲኖች እና ዳይሬክተሮች ጋር የውል ስምምነቱን ተፈራርመዋል።
በፊርማ ስነሥርዓቱ መክፈቻ ላይ የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ከማል ቁልፍ ዉጤት አመላካቾቹ ከዚህ በፊት ከትምህርት ሚኒስቴር ከተላኩት እቅዶች በተጨማሪ በመማር ማስተማሩ፣በጥናት እና ምርምሩ፣በአስተዳደር ሥርዓቱ እና በተቋማዊ የማስፈጸም አቅም ዉጤታማነትን ማረጋገጥ የሚያስችሉ 90 ተቆጥረዉ የተሠጡ ነጥቦች መሆናቸዉን ተናግረዉ ዩኒቨርሲቲዉም ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ባለፈዉ ሳምንት ተፈራርሞ የተቀበላቸዉ ተግባራት እንደሆኑ ገልጸዋል።
የዉጤት አፈጻጸም አመላካች ተግባራቶቹ በሁለተኛዉ ግማሽ አመት የዩኒቨርሲቲዉ የዕቅድ ክለሳ ላይ ተካተዉ ወደ ሥራ እንደሚገባ እና ተቋሙ እንደሚመዘንባቸዉ ፕሬዚዳንቱ ጨምረዉ አብራርተዋል።
ከዚህ በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲዉ
የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ አቶ ታከለ መኮንን የቁልፍ ዉጤት የአፈጻጸም አመላካቾች የትምህርት ተደራሽነትን፣ጥራትን፣ፍትሃዊነትን፣አግባብነትን እና ተቋማዊ የመፈጸም አቅምን ባገናዘበ መልኩ የሚለኩ ሆነዉ የተዘጋጁ መሆናቸዉን ገለጻ አድርገዋል።
ተግባራቱም በቁጥርና በመቶኛ የሚለኩ ሆነዉ በ2017 ዓ.ም ሁለተኛዉ ግማሽ ዓመት ጀምሮ በእቅድ ላይ ተካተዉ ሥራ ላይ እንድዉሉ የሰዉ እና የቁስ ሀይላችንን በእነዚህ ነጥቦች ዙሪያ በማሰለፍ በየዘርፋችን የበኩላችንን ለመወጣት ቆርጠን መነሳት ይኖርብናል ሲሉ አሳስበዋል።
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *