የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት በተዘጋጀዉ የዩኒቨርሲቲዉ የተልዕኮ ልየታ ፍኖተ ካርታ ሰነድ ዙሪያ ግምገማዊ ዉይይት አካሂደዋል፡፡
በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የትኩርት መስክ ልየታ መሰረት የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የተግባር ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ (Applied Science University) ሆኖ መለየቱ ይታወሳል፡፡ በዚህ መሰረት የመስክ ልየታ ሰንድ አዘጋጅ ኮሚቴ (Differentiation Road Map) በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ተዋቅሮ በርካታ ስራዎችን ሲያከናዉን ቆይቷል፡፡
ኮሜቴዉ ያዘጋጀዉን ሰነድ በዛሬዉ ነሐሴ 12/ 2017 ዓ.ም ለዩኒቨርሲቲዉ ማነጅምንት አባላት አቅርቦ ግብዓት እንዲሰጥበት የተደረገ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም ሰነዱ ለመምህራን እና ለአስተዳደር ሰራተኞች እንደሚቀርብ በመድረኩ ተገልጿል፡፡
በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የትኩረት መስክ ልየታ ዋና ዓላማ ዩኒቨርሲቲዎች የአካባቢያቸውን እምቅ የመልማት አቅም፣ ሀብት፣ ሥነ-ምህዳር፣ ኢኮኖሚ ጠቀሜታ እና ተደራሽነትን መሰረት በማድረግ የራሳቸውን ተልዕኮዎች በመለየት እንዲሰሩ በመንግሥት አቅጣጫ ተሰጥቶ እሰተሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Website: www.asu.edu.et
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et