በ10ኛው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል ላይ ሲሳተፍ የነበረው የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ልኡካን ቡድን አሶሳ ከተማ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።
በጅማ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት ከጥር 17 እስከ የካቲት 1/2018 ዓ/ም ድረስ የመላ ኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የስፖርት ዉድድር “ስፖርት ብዝሃነትና ዕውቀት ለልህቀት!” በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ መቆየቱ ይታወሳል።
ልኡካን ቡድኑ በዚሁ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል በተሳተፈባቸው የተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች የስፖርታዊ ጨዋነትን በማሳየት ላደረገዉ ብርቱ ዉድድር የብዙዎችን ቀልብ የሳበ ሲሆን በሴቶች የቼዝ ጨዋታም የወርቅ ሜዳሊያ አግኝቷል፡፡
በዚህ የአቀባበል ስነስርአት ላይ የሚመለከታቸዉ የዩኒቨርሲቲዉ አመራሮችን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችና ሠራተኞች ደስታቸውን በመግለጽ ተቀብለዋቸዋል።
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et


