የዩኒቨርሲቲዉ የሀገበር በቀል እውቀት ጥናት ማዕከል በክልሉ ያሉ ነባር ባህላዊ እሴቶች፣ ክንውኖች፣ ምግቦችና ሌሎች የአከባቢውን ማህበረሰብ እውቀት በማሰባሰብ የማስተዋወቅ ስራ እየሠራ መሆኑን አስታውቋል ፡፡
በዚህ መነሻነት በቤኒሻንጉል ብሔረሰብ ዘንድ ተወዳጅነት ያላቸው የቄንቄስ ባህላዊ ምግብ እና የከርከዴ ባህላዊ መጠጥ በተመለከተ ከአከባቢው ማህበረሰብ መረጃዎችን በማሰባሰብ ለቀጣይ ጥናትና ምርምር እያዘጋጀ መሆኑን በዩኒቨርሲቲው የሀገበር በቀል እውቀት ኦፊሰር የሆኑት መ/ርት አልማዝ ደቼ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ቄንቄስ እና ከርከዴ ከምግብነት ባለፈ የተለያዩ የመድሃንትነት ጠቀሜታ እንዳላቸው የሚገለጽ ሲሆን ሰብሎቹ በተለይ ለጨጓራ ህመም፣ ለደም ግፊት እና ለተመጣጠነ ምግብ እጥረት ህክምና የጎላ ፋይዳ ያላቸው መሆኑም ይነገራል።
ሰብሎቹ የአየር ንብረት መለዋወጥን መቋቋም የምችሉ በመሆናቸዉ ምርታማነትን እና የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ አኳያም ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው መሆኑን የገለጹት ዶ/ር አልማዝ በቀጣይ በነዚህና በመሳሰሉት ሀገርበቀል እውቀቶች ላይ ጥናቶችን በማድረግ ለማህበረሰብ አገልግሎት እንዲውሉ የሚደረግ መሆኑንም ተናግረዋል።
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et
Instagram: https://www.instagram.com/asueduet/#