Assosa University

የትምህርት ፕሮግራሞችን ክለሳ ለማድረግ ለተመረጡ የዩኒቨርሲቲዉ ተማሪዎች የግንዛቤ መፍጠሪያ ስልጠና ተሰጠ

(የካቲት 12/2017 ዓ.ም) በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ፕሮግራሞችን ሀገራዊ እዉቅና (accrediatation) ለማሠጠት እና በተልእኮ ልየታ መሠረት ክለሳ ለማካሄድ ለተመረጡ የዩኒቨርሲቲዉ ተማሪዎች የግንዛቤ መፍጠሪያ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

የአካዳሚክ ፕሮግራም ዳይሬክተር ዶ/ር ወንድም መኩሪያዉ  የስልጠናዉ ዓላማ  ዩኒቨርሲቲዉ በተሠጠዉ ተልዕኮ ልየታ መሰረት የአካዳሚክ ፕሮግራሞችና የስርዓተ ትምህርት  ክለሳ ለማድረግ ተማሪዎች ግንዛቤ እንዲኖራቸዉ ለማድረግ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በዉይይቱ ከተለያዩ ትምህርት ክፍሎት የተዉጣጡ ተማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን በትምህርት ጥራት እና ማሻሻል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት በዶ/ር ገለታ ፍቃዱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዉ ተሰጥቷል።፡፡

በትናንትናዉ ዕለት ለተመረጡ ትምህርት ክፍል ተጠሪ መምህራን ተመሳሳይ ስልጠና መሰጠቱን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን

Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X

WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P

Facebook: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial

Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk

Email: pir@asu.edu.et

Instagram: https://www.instagram.com/asueduet/#

 

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *