ዩኒቨርሲቲዉ ነባር ተማሪዎቹን ተቀብሎ ሰላማዊ የመማር ማስተማሩን ሥራ ከጀመረ ሰነባብቷል። አሁን ደግሞ ከፊት ለፊታችን ህዳር 16 እና 17/2017 ዓ.ም አዲስ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል።
ከዚህ ጋርም ተያይዞ በተማሪዎች መሠረታዊ አገልግሎት ድን ሥር ከሚገኙ የተማሪዎች ምግብ ቤት ሠራተኞች፣ የመኝታ ቤት ተቆጣጣሪዎች ፣ የክሊኒክ እና የተማሪዎች ስብዕና ግንባታ ሠራተኞች ጋር ስለ አገልግሎት አሠጣጥ በዛሬዉ ዕለት አጭር ዉይይት ተካሂዷል።
ዉይይቱን የመሩት የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጌታቸዉ አለሙ እና የተማሪዎች አገልግሎት ዲን መ/ር ጌታቸዉ ገለታ ናቸዉ።
በዉይይቱ ላይ ዶ/ር ጌታቸዉ አገልግሎት መስጠት በባህሪዉ ለሌሎች ራስን መስጠት በመሆኑ ዋጋዉ በገንዘብ የሚተመን ሳይሆን ማገልገል የህሊና እርካታ የሚያስገኝ ተግባር ነዉ ብለዋል።
መ/ር ጌታቸዉም ተማሪዎቻችን እኛን እናትና አባት አድርገዉ የሚኖሩ ስለሆኑ በቻልነዉ ልክ ልናገለግላቸዉ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
ሠራተኞቹም ዉጤታማ ሥራዎችን ለመሥራት መስተካከል ቢችሉ ያሉአቸዉን ሀሳብና አስተያየት ሰጥተዋል።
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et
Instagram: https://www.instagram.com/asueduet/#