የዩኒቨርስቲው ተማሪዎችን ማህበራዊ ግንኙነት ማጠናከር እንዲሁም የባህል ልውውጥን ዓላማ ያደረጉ የኪነጥበብ ስራዎች ቀረቡ።
የሀገር በቀል እውቀት ጥናት ኦፊሰር ዶ/ር አልማዝ ደቼ በመክፈቻ ንግግራቸው “ተማሪዎች በሚማሩበት አካባቢ ያለውን ባህል እንዲያውቁ እንዲሁም የራሳቸውን ባህል እንዲያስተዋውቁ እድሉን ለመፍጠርና አብሮነታቸውን ለማጠናከር እንዲህ አይነት መድረኮች ትልቅ ሚና ይኖራቸዋል” ብለዋል:: ዶ/ር አልማዝ አክለውም ዝግጅቱን ላስተባበሩ እና ተማሪዎች እና ባለሙያዎች ከፍ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በዝግጅቱ ላይ ዬኬ ትውፊታዊ ቲያትርን ጨምሮ ግጥም፣የባህላዊ አልባሳት ትርዒት እና ባህላዊ ውዝዋዜዎች ለታዳሚው ቀርበዋል።
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et
Instagram: https://www.instagram.com/asueduet/#