Assosa University

የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረገዉ ጥረት መደገፍ እንደሚገባ ተገለፀ

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንና የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የግቢው መምህራንና ሰራተኞች እንዲሁም ተማሪዎች በተገኙበት እለቱን በሚዘክሩ በተለያዩ ሁነቶች አክብሯል።
 
የክብረ በአሉን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ መ/ር መርቀኒያ አሊ ሲሆኑ ለአደዋ ድል የሴቶች ተሳትፎ ትልቅ ሚና እንደነበዉ አዉስተዉ በዩኒቨርሲቲዉ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ተጨባጭ ለውጦች መመዝገባቸውን ተናግረዋል፡፡
 
በቀጣይም ሴቶችን በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መስኮች ተጠቃሚነታቸውን ለማጠናከር የሁሉም አካላት የጋራ ርብርብ እንደሚጠይቅ ገልፀዋል፡፡
 
በፕሮግራሙ የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዘዳንት ዶ/ር አብዱልሙህሰን ሀሰን መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በሀጋረችን የሴቶችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
 
ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን የበዓል ቀን ብቻ ሳይሆን ሴቶች በአደዋ ጦርነት ላበረከቱት ተጋድሎ የምንዘክርበት ዓለም አቀፍ ንቅናቄ በመሆኑ የሴቶችን ቀጣይ ትምህርት እና ተሳትፎ ብሎም የወንዶችን አጋርነት የምናጠናክርበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
ዶ/ር አብዱልሙህሰን አክለዉም ድህንነትን እንደ አደዋ ጦርነት ድል ለማድረግ ሴቶችን ሁሉም በተሰማራበት የስራ ዘርፍ ሁለንተናዊ ተሳታፊና ተጠቃሚ በማድረግ እንዲሁም ፅናትን በመላበስ ዉጤታማ ስራ በመስራት ሀገራችን ለያዘችሁ የእድገት ጉዞ የበኩላችንን አስተዋፅኦ እንድናበርክት ሲሉ ጠይቀዋል፡፡፡
 
ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን በሀገራችን ለ49 ጊዜ በዩኒቨርሲቲያችን ደግሞ ለ13ኛ ጊዜ “ፈጣንና ቀጣይነት ያለዉ ሁሉን አቀፍ ለዉጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል“በሚል መሪ ቃል ተከብሯል፡፡
 
በበዓሉ በዶ/ር ምትኬ ልየዉ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዓል መከበር አስፈላጊነትና የሴቶች ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነት እና በዶ/ር አበበ አኖ በአደዋ ጦርነት የሴቶች ሚና በሚሉ ርዕሶች የመነሻ ሰነዶች ቀርዉ በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
 
በመጨረሻም በትምህርታቸዉ ጥሩ ዉጤት ላስመዘገቡ የዩኒቨርሲቲዉ ሴት ተማሪዎች እውቅና እና ሽልማት ተረክቷል።
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *