Assosa University

የሥርዓተ ፆታ ትንኮሳን ለመከላከል በጉዳዩ ላይ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚገባ ተጠቆመ

(አሶሳ ዩኒቨርሲቲ፣ የካቲት 18/ 2017 ዓ.ም) ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣዉ የሥርዓተ ፆታ ትንኮሳን ለመከላከል ባለድርሻ አካላት ለህብሰተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ ላይ ማትኮር እንደሚገባ ተገልጿል።
 
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ከቤ/ጉ/ክ/መ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ጋር በመተባበር በሥርዓተ ፆታ ትንኮሳ ላይ ከአሶሳ ዞን ወረዳዎች የተወጣጡ ባለሙያዎች ለሁለት ቀናት ሲሰጥ የነበረዉ ሥልጠና ተጠናቋል።
 
የማጠቃለያ ፕሮግራሙ ላይ በሥርዓተ ፆታ ትንኮሳ መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ፣ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝነት እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት እስከ ታችኛዉ የማህበረሰብ ክፍል ማድረስ አስፈላጊነት እና የዩኒቨርሲቲዉ እገዛ በስፋት ተነስቶ ዉይይት ተደርጎባቸዋል።
 
ከሠልጣኞች የተነሱ ጥያቄዎች እና ሀሳቦች ላይ የማህበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ተፈራ ተሾሜ ምላሽ የሰጡ ሲሆን ዩኒቨርሲቲዉ የማህበረሰቡን ችግር መሠረት በማድረግ ለሚቀርቡ ጉዳዮች ትኩረት እንደሚሰጥ ጠቁመዋል። በሥርዓተ ፆታ ትንኮሳ መከላከል ላይም ከባለድርሻ አካላት ጋር አብሮ መሥራት አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን

Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X

WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P

Facebook: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial

Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk

Email: pir@asu.edu.et

Instagram: https://www.instagram.com/asueduet/#

 

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *