(የካቲት 1/2017 ዓ/ም) በኩሶ ኢንተርናሽናል ዩ-ገርልስ 2 ፕሮጀክት ላለፉት አራት ዓመታት ዕገዛ እያደረገ ያስተማራቸዉን የ2016 ዓ.ም የ12 ክፍል ብሔራዊ ፈተና የወሰዱ ሴት ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲዉ በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ፡፡
በምርቃት ፕሮግራሙ ንግግር ያደረጉት የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጅ ሽግግር ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር አብዱልሙህሰን ሀሰን ዩኒቨርሲቲዉ የክልሉን ማህበረሰብ ሁለተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
ዶ/ር አብዱልሙህሰን ሀሰን አክለዉም ዩኒቨርሲቲዉ ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም በጤና፣ በግብርናና በትምህርት እንዲሁም በነፃ የህግ አገልግሎት ዙሪያ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዉ በቀጣይ ከካናዳ መንግስት ጋር ዩኒቨርሲቲዉ በጋራ መስራት እንደሚፈልግ ተናግረዋል፡፡
በፕሮግራሙ በኢትዮጵያ የካናዳ አምባሳደር ጆሸዋ ታባ፣ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ክቡር አቶ በሽር እና የሴቶች ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ክብርት አለምነሽ ይባስ ተገኝተዉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ኩሶ ኢንተራናሽናል ላለፉት አራት ዓመታት በክልሉ በተመረጡ ሰባት የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች 1650 ሴት ተማሪዎችን ድጋፍ በማድረግ ትምህራታቸዉን እንዲከታተሉ ያደረገ ሲሆን በ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍ ብሔራዊ ፈተና የወሰዱ 473 ሴት ተማሪዎችን በዛሬዉ ቀን በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል፡፡
በመጨረሻም በተለያዩ ስራዎች በመሳተፍ ላበረከተዉ አስተዋጽኦ ለአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የምስጋና ሰርቲፊኬት ተበርክቷል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et
Instagram: https://www.instagram.com/asueduet/#