Assosa University

የመንገድ ደህንነት የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነዉ

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በማህበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት በመንገድ ትራፊክ ደህንነት መመሪያና አፈፃፀም ዙሪያ ለትራፊክ ፖሊሶችና መንገድ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡
ተፈራ ተሾመ (ዶ/ር) የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክተር በስልጠናዉ መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር ስልጠናዉ በመንገድ ትራፊክ ደህንነት ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ የትራፊክ ፖሊሶችንና የመንገድ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎችን አቅም ለማጎልበትና ህግና ደንብን ተከትሎ አግባብነት ያለዉ አገልግሎት ለማህበረሰቡና ለአሽከርካሪዎች እንዲሰጡ የሚያስችል ስልጠና እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
ዶ/ር ተፈራ ተሾመ አክለዉም የትራንስፖርት ስርዓቱን ሰላማዊና ከአደጋ የፀዳ እንዲሆን አሽከርካሪዎችም ሆነ ማህበረሰቡ አስከፊዉን የትራፊክ አደጋ ለመከላከልና ለመቆጣተር ሁሉም የድርሻዉን እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡
በስልጠናዉ ከአሶሳ፣ ከአቡርሃሞ እና ከኡራ ወረዳዎች የተዉጣጡ 40 የትራፊክ ፖሊሶችና የመንገድ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛል፡፡
ስልጠናዉ በመምህር ተገኝ ሞታ እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን ስልጠናዉ መሰጠቱ ዘላቂ የሆነ የመንገድ ትራፊክ ደህንነትን ለማረጋገጥና አደጋዎችን ለመቀነስ እንደሚያስችል ተገልጧል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *