የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል የ2017 ዓ.ም ዓመታዊ የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2018 ዓ.ም መነሻ ዕቅድ ዙሪያ ግምገማ አድርገዋል፡፡
የ2017 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2018 ዓ.ም መነሻ ዕቅድ በስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ አቶ ታከለ መኮነን የቀረበ ሲሆን ሪፖርቱ በአራቱም ዘርፎች የተከናወኑ አበይት ተግባራት ዝርዝር፣ በትግበራ ሂደት ያጋጠሙ ችግሮች፣ የተወሰዱ የመፍትሔ አቅጣጫዎችና የተገኙ ውጤቶች በሚያሳይ መልክ ተተንትነው ቀርበዋል።
በመድረኩ የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ከማል አብዱራሂም በ2017 ዓ.ም የተሻለ አፈፃፀም የተመዘገበበት ዓመት መሆኑን ገልፀው ይህ ሥራ አሁንም ከዚህ በበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉን አቅፍ ርብርብ ይደረጋል ብለዋል፡፡ እንደ አጠቃላይ በግዥ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችንም በመዝጋት የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡
የካዉንስል አባላቱ በቀረቡ የአፈፃፀም ሪፖርቶች እና የ2018 ዓ.ም መነሻ እቅድ ላይ በሰፊዉ ተወያይተዋል፤ በርካታ ጥያቄዎች እና አስተያየቶችም ቀርቦ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et
Instagram: https://www.instagram.com/asueduet/#