(ህዳር 04/2014 ዓ.ም) የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማር ሥራው በተጨማሪ ለአቅመ ደካሞች፣ ለሴቶች፣ ለሕፃናት እና ተጋላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ሦስት ማዕከላትን በመክፈት ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ሥራዎችን በመስጠት ላይ መሆኑ ይታወቃል። የዩኒቨርሲቲው የሕግ ትምህርት ቤት ከቤ/ጉ/ክ/መ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ቢሮ ጋር በመተባበር የነፃ የሕግ ድጋፉ አገልግሎት የ2013 በጀት አመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለመገምገምና የቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ህዳር 04/2014 ዓ.ም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ውይይት አካሂዷል። የዩኒቨርሲቲው የምር/ማህ/አገ/ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሀይማኖት ዲሳሳ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት የዩኒቨርሲቲውን ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ፕሮግራም አጠናክሮ ለማስቀጠል ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩሉን ኃላፊነት በመወጣት የፍትህ ተደራሽነቱን ማሳካት እንደሚገባ ጠይቀዋል። የውይይቱ ዓላማም ተጋላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች የምንሰጠውን ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት ለማጠናከርና የፍትህ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን የጉለጹት የቤ/ጉ/ክ/መ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ዋና ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ሠይድ ባበክር ናቸው። በመድረኩም ሦስት መነሻ ጽሑፎች በዩኒቨርስቲው የህግ ምሁራንና በክልሉ የህግ ባለሙያ ቀርበዉ ዉይይት ተደርጎባቸዋል። በውይይቱ ማጠቃለያ ወቅት የተገኙት የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ረዳት ፕሮፌሰር አበራ በይሳ ይህ የውይይት መድረክ መዘጋጀቱ ተጋላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች የምንሰጠውን አገልግሎት በጋራ ለመፈፀምና በሥራው ሂዴት ውስጥ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በቀላሉ ለመፍታት ያስችለናል ሲሊ ተደምጠዋ። ረዳት ፕሮፌሰር አበራ በይሳ አያይዘውም ዩኒቨርሲቲያችን ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎቱን በሁሉም ወረዳዎች ተደራሽ ለማድረግ ከምንግዜውም በላይ ተግቶ እንደሚሰራ ገልፀዋል።