Assosa University

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የ2018 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ተማሪዎችን እየተቀበለ ነዉ

(አሶሳ ዩኒቨርሲቲ፣ ታህሳስ 2/2018 ዓ/ም) አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አዲስ የተመደቡ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው።
 
የዩኒቨርሲቲዉ የተማረዎች አገልግሎት ዲን የሆኑት መ/ር ደሳለኝ አየለ እንደገለፁት ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ወደ ዪኒቨርሲቲው የተመደቡ የአቅም ማሻሻያ ተጠቃሚ ተማሪዎች በሰላም እየገቡ እንደሆነ ገልጸዋል።
 
የተማሪዎችን ቅበላ ፕሮግራም በተሳካ ሁኔታ ለማስኬድ ቀደም ብሎ የቅበላ ኮሚቴ በማቋቋም ፣ በርካት ስራዎችን መሰራቱን መ/ር ደሳለኝ አየለ ተናግረዉ ተማሪዎች ሳይቸገሩ ወደ ዩኒቨርሲቲዉ እንዲገቡ ኮሚቴው የተለያዩ እገዛዎችን በማድረግ ያለ ምንም እንግልት እስከ መኝታ ክፍሎቻቸው የማድረስ ስራዎች እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል ።
 
መ/ር ደሳለኝ አያይዘውም በ2018 ዓ/ም ለዩኒቨርሲቲዉ ከ1670 በላይ የአቅም ማሻሻያ ተጠቃሚ ተማሪዎች እንደተመደቡ ገልፀዉ ዩኒቨርስቲውን ለተቀላቀሉት አዲስ የአቅም ማማሻያ ተማሪዎችም እንኳን ወደ ሁለተኛ ቤታችሁ ወደ ሆነው የሰላም፣ የፍቅር እና የጥበብ መፍለቂያ ዩኒቨርሲቲ በሰላም መጣችሁ ብለዋል።
ተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማህበራዊ ትስስር ገፆቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *