Assosa University

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ከቤጉ ደቨሎፕመንታል ግሩፕ ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለዉን የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ

መጋቢት 28/2015 ዓ.ም

ዩኒቨርሲቲዉ በተልእኮ ልየታ መሰረት በአፕላድ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ ከተለየ ወዲህ በክልሉ እና በሀገር ደረጃ ከሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነቶችን ማድረግ ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡

በመሆኑም በዛሬዉ ዕለት ከቤጉ ደቨሎፕመንታል ግሩፕ ከተሰኘ በኮንስትራክሽን፣ በማዕድን ልማት እና በግብርና ልማት ዘርፍ ከተሰማራ መንግታዊ ድርጅት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

የዉል ስምምነቱን በዩኒቨርሲቲዉ በኩል የዩኒቨርሲቲዉን ፕሬዝዳንት ተወካይና የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት  ዶ/ር አብዱልሙስን ሀሰን የፈረሙ ሲሆን በቤጉ ደቨሎፕመንት ግሩፕ በኩል ደግሞ የልማት ድርጅቱ ሀላፊ አቶ መንግስቱ ቴሶ ፈርመዋል፡፡

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

facebook: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial

telegram: https://t.me/assosauniversity_official website: https://www.asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *