አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ከልማት ለሁሉም በጎ አድራጎት ማህበር ጋር በመተከል ዞን አብሮ ለመስራት የሚያስችለው የመግባቢያ ስምምነት ዛሬ ተፈራርሟል።
የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡመር ሸሪፍ እንደገለፁት ዩኒቨርሲቲዉ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
ባለፉት 6 ወራትም ከአስራ አምስት በላይ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ጋር አብሮ ለመስራት ስምምነት ፈፅሞ ስራዎች እያከናወነ መሆኑን ገልጠዉ ተቋሙ የሰለጠነ የሰው ሀይል በማቅረብ ለክልሉ አቅም መሆኑን ዶ/ር ኡመር አክለው ተናግረዋል ።
የሁለቱ ተቋማት ውል ስምምነት በክልሉ የፍትህ ተደራሽነትን በማሻሻል ለተፈናቃዮች፣ ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞች እና ለተጋላጭ ወጣቶች የፍትህ ተደራሽነትን ለማሻሻል እና የእውቀት ልውውጥ፣ በስልጠና እና በአቅም ግንባታ ዘርፎች የተቋማትን አቅም ለማጠናከር እንደሆነ ተገልጧል፡፡
የመግባቢያ ስምምነቱ በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በዶ/ር ኡመር ሸሪፍ እና የልማት ለሁሉም በጎ አድራጎት ኦፊሰር በሆኑት በአቶ ፈንታሁን መለሰ ተፈርሟል።
በስነስርዓቱ ላይ የዩኒቨርሲቲዉ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክተሮች እና የማህበሩ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et



