ህዳር 03/2017 ዓ.ም
የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ዛሬ ህዳር 03/2017 ዓ.ም ባካሄደዉ ስብሰባዉ አራተኛዉን የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ለዶ/ር መልካሙ ዴረሳ ሰጥቷል፡፡
ዶ/ር መልካሙ ዴረሳ በምርምር፣ በማህበረሰብ አገልግሎት ሥራዎች እና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መስፈርቶችን አሟልተዉ በመገኘታቸዉ ማዕረጉ ተሰጥቷቸዋል፡፡
ዶ/ር መልካሙ ዴረሳ በዩኒቨርሲቲዉ በመምህርነት ሙያ፣ በተመራማሪነት እና በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ያገለገሉ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የዩኒቨርሲቲዉ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነዉ በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡
በዚህ አጋጣሚም ዩኒቨርሲቲዉ ሴኔቱ የተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸውን ደ/ር መልካሙ ዴረሳን እንኳን ደስ አለዎት ለማለት ይወዳል።
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et
Instagram: https://www.instagram.com/asueduet/#