የዩኒቨርሲቲዉ የማህበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክቶሬት በኩርሙክ ወረዳ ዱልሸታሎ ቀበሌ የታዳጊዎች ለአራት ዓመት የሚቆይ የእግር ኳስ ፕሮጀክት በዛሬዉ ዕለት አስጀምሯል።
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ ፕ ዶ /ር አብዱልሙህስን ሀሰን ሲናገሩ ስፖርት ጤና እና ፍቅርን ከማስፈኑ በተጨማሪ ሀገርን የሚገነባ ዘርፍ መሆኑን በመረዳት ዩኒቨርሲቲያችን ከሚያከናዉናቸዉ በርካታ የማህበረሠብ አገልግሎት ፕሮጀክቶች መካከል የዱልሸታሎ እግር ኳስ ፕሮጀክት አንዱና የዘመኑ ትልቅ ፕሮጀክት መሆኑን በማስገንዘብ ከዛሬ ቀን ጀምሮ የመጣዉን ትጥቅ በመጠቀም ስፖርቱ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል።
በተመሳሳይ በቦታዉ የተገኙት የቤ /ጉ/ ክ/ መ /ስፖርት ኮሚሽኔር አቶ ኢብራሂም ስፖርት ልማት ነዉ ልማትነቱን በዱልሸታሎ ቀበሌ እዉን ለማድረግ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በቁርጠኝነት የታዳጊ ህፃናት የእግር ኳስ ፕሮጀክት ማስጀመሩን አድንቀዉ እግር ኳሱን እግር ብቻ የሚጫወተዉ ሳይሆን ጭንቅላት ጭምር በመሆኑ ልጆቻችን ከተለያዩ ጎጅ ሱሶች በማራቅ ስፖርቱን ሱስ እንድያደርጉ መሠራት ይኖርበታል ብለዋል።
በተጨማሪም ሀላፊዉ 25 ዓመት ሳይሞላቸዉ ከስፖርት ራሳቸዉን የሚያገሉ ተስፋ የተጣለባቸዉ ወጣቶች ለአርአያነት የማይሆኑ መሆናቸዉን ገልጸዉ በፕሮጀክቱ የታቀፉ ታዳጊዎች ኳስን ማባረር ብቻ ሳይሆን የእግር ኳስ ህግንና ሳይንሱን ማወቅ የመጀመሪያ ተግባራቸዉ ማድረግ እንዳለባቸዉ አሳስበዋል።
የፕሮጀክት ማስጀመሪያ ፕሮግራሙ የተለያዩ የእግር ኳሶች፣ታኬታ ጫማዎች፣ ገምባሌዎችን እና ቱታዎችን ለ30 ታዳጊ ወጣቶች እንዲሁም ለአንድ አሠልጣኝ በማስረከብ ተጠናቋል
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Facebook: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et
Instagram: https://www.instagram.com/asueduet/#