Assosa University

በዩኒቨርሲቲው የኢፍጣር መርሃ-ግብር ተካሄደ

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሮመዳን ፆም ምክኒያት በማድረግ የዩኒቨርስቲው አመራሮች ከተማሪዎች ጋር የኢፍጣር መርሃ ግብር በተማሪዎች ምግብ ቤት አካሂደዋል::
 
በመርሃ ግብሩ ላይ የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ መ/ር ንጋቱ ሀምቢሳ ተገኝተው የፍቅርና የመተሳሰብ ጊዜ ለሆነው የሮመዳን ወር የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።
 
እንዲሁም የተማሪዎች መሰ/አገ/ ዲን መ/ር ጌታቸው ገለታ እና የሴ/ት ማህ/ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ መ/ርት መርቀኒያ አሊ በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ተማሪዎችን አበረታትዋቸዋል።
 
በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት ተማሪዎችም ለተደረገላቸው የአፍጠር ፕሮግራም ተደስተው ዩኒቨርሲቲውን አመስግነዋል።
 
 
የተቋሙን ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፤
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *