Assosa University

በዩኒቨርሲቲዉ 2017 ዓ/ም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የስነ ምግባር አምባሳደርን ለመምረጥ የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሄደ

የፌደራል ስነ ምግባር እና የጸረ ሙስና ኮሚሽን በሃገር አቀፍ ደረጃ ለሚያካሂደው የ2017 ዓ.ም የስነ ምግባር አምባሳደር የጥያቄና መልስ ውድድር ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎችን ለመምረጥ የተማሪዎች ጥያቄና መልስ ውድድር አካሄደ።
 
በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር መልካሙ ደሬሳ ሲሆኑ በንግግራቸው ስነ ምግባርን በመላበስ በተሰማራንበት የስራ መስክ ሁሉ ዉጤት በማሰመዝገብ ኃላፊነትን መወጣት እንደሚገባ ገልፀዋል።
 
በውድድሩ ቀደም ሲል የተሰጠዉን የጹህፍ ፈተና ያለፉ 5 ወንድ እና 1 ሴት በድምሩ 6 ተወዳዳሪ ተማሪዎች ተሳትፈዋል። በዚህም ተማሪ ፈይሳ ባልቻ 1ኛ፣ ተማሪ ቀነኒ ሙሉነህ 2ኛ እንዲሁም ተማሪ አቤል አላምነህ 3ኛ በመዉጣት የሞባይል ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
1ኛ በመውጣት ውድድሩን ያሸነፈው ተማሪ ፈይሳ ባልቻ የፌደራል ስነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን በሃገር አቀፍ ደረጃ በሚያካሂደው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የስነምግባር አምባሳደር የጥያቄና መልስ ውድድር ላይ የሚሳተፍ ይሆናል፡፡
 
የተቋሙን ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፤
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *