Assosa University

በዩኒቨርሲቲዉ የግንባታ ዉል አስተዳደር ዙሪያ ዉይይት ተደረገ

(የካቲት 17/2015 ዓ/ም) የግንባታ ዉል አስተዳደርን አስመልክቶ የዩኒቨርሲቲዉ የግንባታ አማካሪዎች፣ የፕሮጀክት ጽ/ቤት እና በቀጥታ ከሚመለከታቸዉ የስራ ክፍል ሃላፊዎች ጋር ዉይይት ተደረጓል፡፡

ለዉይይት መነሻ የሚሆን በህግ ት/ቤት መምህር በሆኑት ዘሪሁን ይታየዉ የኢትዮጵያ የግንባታ ዉል አስተዳደር እና የጨረታ ህግን አስመልክቶ የወጡ አዋጆች፣ መመሪያዎች እና ደንቦችን ቀርበዉ በሰፊዉ ዉይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

አማካሪዎች፣ የፕሮጀክት ጽ/ቤት ሰራተኞች እና በቀጥታ የሚመለከታቸዉ ስራ ክፍሎች በተቋራጮች የሚከናዉኑ የግንባታ ስራዎች የግንባታ ዉል እና መመሪያዎችን በመጠበቅ መስራት እንደሚገባ የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ከማል አብዱራሂም በዉይይቱ ላይ አሳስበዋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *