Assosa University

በዩኒቨርሲቲዉ የአባይ ዘመን ትዉልድ በሚል መሪ ቃል የኪነ ጥበብ ምሽት ተካሄደ

ዩኒቨርሲቲዉ ከቤኒሻንጉል ጉ/ክ መንግስት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባባሪያ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር የኪነ ጥበብ ምሽት መርሃ ግብር ያዘጋጀ ሲሆን የክልል ፣የዞን፣የከተማ አስተዳደር እና የዩኒቨርሲቲዉ አመራሮች ፣የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች እንዲሁም የዩኒቨርሲቲዉ መምህራን እና ተማሪዎች በተገኙበት ተካሂዷል።
 
የመርሃ ግብሩ ዓላማ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የተጀመረበትን 14 ኛ ዓመት ዋዜማ ምክኒያት በማድረግ እና የግንባታዉ የመጨረሻዉን ምዕራፍ ለማጠናቀቅ በክልሉ የገቢ ማሰባሰቢያ ማስጀመሪያ ቅስቀሳ ለማድረግ ነዉ ።
በመርሃ ግብሩ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር አብደልሙህሲን ሀሰን አባቶቻችን የአድዋ ታሪክን ሰርተዉ ያለፉ ሲሆን እኛ የዚህ ዘመን ትዉልድ ደግሞ ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን በመገንባት ታሪክ እየሠራን መሆኑን ገልጸዉ ዩኒቨርሲቲዉ ለግድቡ ግንባታ ገቢ ከማሰባሰብ በተጨማሪም የአባይ ተፋሰስን ለማልማት በጥናት እና ምርምር የተደገፈ ሥራ ለመስራት የምርምር ማዕከል ለማቋቋም በዝግጅት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።
 
በመድረኩም እስካሁን ግንባታዉን ለማከናወን የተሠሩ ሥራዎች ተዳሠዉ በቀጣይ መሠራት የሚገባቸዉ ጉዳዮች በዉይይቱ ላይ ተመላክተዋል።
ከዉይይቱ በተጨማሪም የተለያዩ አባይን የሚመለከቱ የኪነ ጥበብ ሥራዎች ቀርበዋል።
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *