Assosa University

በዩኒቨርሲቲዉ የነጭ ሪቫን ቀን ተከበረ

የነጭ ሪቫን ቀን “የሴቷ ጥቃት የኔም ነዉ ዝም አልልም” በሚል መሪ ቃል በዩንቨርሲቲው ተከበረ።
በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በመሆናቸው በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች እንዲወገዱ ወንዶችም የትግሉ አጋርና ባለቤት መሆን እንዳለባቸው ዝግጅቱን በንግግር የከፈቱት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካትቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ መምህርት መርቀንያ አሊ ተናግረዋል።
ሥራ አስፈሚዋ አክለውም የጥቃቱን አስከፊነት በመረዳት ጥቃት አድራሾች ማስተማሪያ የሚሆን እርምጃ እንዲወሰድባቸው ማገዝ እና ተጠቂዎችም ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ የ ሁላችንም ኃላፊነት ነው ብለዋል።የሰብአዊ መብት ክበብ አስተባባሪ መ/ር ዘላለም ታደሰ በበኩላቸዉ ክበቡ ተማሪዎች መብትና ግዴታቸዉን አዉቀዉ ለፆታዊ ጥቃት ተጠቂዎች ተሟጋች እንዲሆኑ ግንዛቤ የመፍጠር ዘመቻዎች ላይ እእየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
በበዓሉ ላይ ወንዶች ነጭ ሪቫን በማድረግ አጋርነታቸውን የገለፁ ሲሆን የመወያያ ፅሁፍ በተማሪ ትዕግስት ፈንታዉ እና በተማሪ ምህረት አዱኛ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡ቀኑን በማስመልከትም በተማሪዎች የተለያዩ የስነ-ፅሁፍህፎች ቀርበዋል፡፡
ዝግጅቱን የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካትቶ ትግበራ ሥራ አስፈፃሚ እና በሰባዊ መብት ክበብ አባላት አስተባባሪነት የተዘጋጀ ሲሆን፤ የነጭ ሪቫን ቀን ሲከበር በአለም አቀፍ ደረጃ ለ33ተኛ በአሶሳ ዩኒቨርስቲ ደግሞ ለ4ተኛ ጊዜ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል።
 
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *