Assosa University

በዩኒቨርሲቲዉ ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን ተከበረ

ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን ለ13ኛ ጊዜ “የአካል ጉዳተኞችን የመሪነት ሚና በማጉላት አካታች እና ዘላቂ ልማትን እናረጋግጥ” በሚል መሪ ቃል በስፖርታዊ ዉድድሮች በዩኒቨርሲቲዉ ተከብሮ ዉሏል፡፡
ስፖርታዊ ዉድድሩን የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ሀላፊ መ/ር ንጋቱ ሀምቢሳ፣የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ እና አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ መ/ርት መርቀኒያ አሊ እንድሁም ዶ/ር መሰረት ሙሉ ጌታ አስጀምረዉታል፡፡
መ/ር ንጋቱ እና መ/ርት መርቀኒያ ዕለቱ በስፖርታዊ ጨዋታዎች መከበሩ ስፖርት የሠላም እና የአብሮነት ማምጫ መንገድ በመሆኑ አንድሁም አካል ጉዳተኝነት አጋጣሚ እንጅ አለመቻል አለመሆኑን ለማስገንዘብ ታልሞ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል።
በዓሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ 32 ኛ፣ በሀገራችን ለ 31 ኛ እንድሁም በዩኒቨርሲቲዉ ለ 13 ኛ ጊዜ በመከበር ላይ ይገኛል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *