ለዩኒቨርሲቲዉ ካዉንስል በ2018 ዓ.ም ቁልፍ ዉጤት አመላካች (KPIs) አፈጻጸም እና የቀሪ ግማሽ አመት የትኩረት አቅጣጫን አስመልክቶ ግምገማዊ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
በግምገማ ዉይይቱ ላይ የዩኒቨርሲቲዉ የ2018 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የቁልፍ ዉጤት አመላካች አፈጻጸም እና በትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠ የአፈጻጸም ግብረ መልስ በስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ በአቶ ታከለ መኮንን ከቀረበ በኋላ የቁልፍ ዉጤት አመላካች የቀጣይ ግማሽ ዓመት የትኩረት አቅጣጫ እና ግምገማ በዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ከማል አብዱራሂም ቀርቦ ጥልቅ ዉይይት ተደርጎበታል፡፡
ዩኒቨርሲቲዉ 99 ቁልፍ ዉጤት አመላካች (KPI) አቅዶ በተቀመጠላቸዉ ቤዝ ላየን መሰረት በመማር ማስተማሩ ፣በምርምሩ እና ቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም በአስተዳደር አፈጻጸማቸዉ በትምህርት ሚኒስቴር በኩል የተሰጡ ከፍተኛ፣መካከለኛ እና ዝቅተኛ የሚሉ ግብረ መልሶች ለካዉንስል አባላቱ ቀርበዋል።
በዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት በኩል በቀጣይ ቀሪ ግማሽ ዓመት የሪፎርም ሥራዎች ላይ መተኮር እንዳለበት፣ ለምናከናዉናቸዉ ማንኛዉም ስራዎች መረጃዎች ማጠናከር እንደሚገባ፣ተማሪ እኛን መርጦ እንድመጣ የመማር ማስተማሩ ሥራዉ ጤታማ እንድሆን ማድረግ፣አስተዳደራዊ እና አገልግሎት አሰጣትን ቀልጣፋ ማድረግ፣የማህበረሰብ ጉድኝት ስራዎችን እንዲሁም የዉስጥ ገቢን ማሳደግ የቀጣይ የ6 ወራት እቅድ ትኩረት የሚያስፈልጋቸዉ ተግባራት የሚሉት በዋነኛነት ተመላክተዋል፡፡
እነዚህ የዉይይት መነሻ ሀሳቦች ከቀረቡ በኋላ በካዉስሉ አባላቱ መነሳት ያለባቸዉ ሀሳብና አስተያየት ተነስተዉ ጥልቅ ዉይይቴ ተደርጎባቸዉ መድረኩ ተጠናቋል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et





