ለአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ለ2015 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች መሰረታዊ የኮምፒዉተር ክህሎት ማሳደጊያ ስልጠና ከመጋቢት 26-27/2015 ዓ.ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡ ስልጠናዉ እየተሰጠ የሚገኘዉ በሶስት ኮሌጆችና አንድ ትምሀርት ቤት ስር ለሚገኙ ለማህበራዊ እና ስነሰብ፣ለቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ለተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ እና ለህግ ትምህርት ቤት ለ2015 ተመራቂ ተማሪዎች ነዉ፡፡
የስልጠናዉ ዋነኛ ዓላማም ተመራቂ ተማረዎቹ ለሚወስዱት የመዉጫ ፈተና (Exit Exam) ሊያዘጋጃቸዉና ሊያግዛቸዉ የሚችል የኮምፒዉተር ክህሎት ማሳደግ እንደሆነ የኮምፒዉቲንግና ኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ ዲን የሆኑት ዶ/ር ሻምበል ፈረደ ተናግረዋል፡፡ ስልጠናዉ እየተሰጠ የሚገኘዉ በኮምፒዉቲንግና ኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ መምህራን ሲሆን በቀጣይም ለግብርና ተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ኮሌጅ እና ለጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተመራቂዎች ስልተናዉ ይሰጣል ተብሏል፡፡
የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
face book: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial
Telegram: https://t.me/assosauniversity_official
Website: https://www.asu.edu.et