Assosa University

በአደንዛዥ ዕፅ አስከፊነት ዙሪያ ለወጣት ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ነዉ

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ከቤ/ጉ/ክ/መ/ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ጋር በመተባበር ከአሶሳ ዞን ከሁሉም ወረዳዎች ለተዉጣጡ ወጣት ባለሙያዎች በአደንዛዥ ዕፅ፣ ህገወጥ ፍልሰትና ስደት አስከፊነት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ነዉ፡፡
 
በስልጠናዉ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የማህበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክተር ዶ/ር ተፈራ ተሾመ ሲሆኑ አደንዛዥ ዕፅ ፣ ህገወጥ ፍልሰትና ስደት እንደ ሀገር አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን አንስተዉ የነገ ሀገር ተረካቢና የልማት ሀይል የሆነዉን ወጣት በዚህ ችግር መያዝ ከግለሰቡ አልፎ ቤተሰብ ብሎም ሀገርን የሚጎዳ በመሆኑ ነገሮቸን አመዛዝኖ ሚያይ ባለ ራዕይ ትዉልድ ለመፍጠር በትብብር መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
 
ስልጠናዉን ያስጀመሩት የምርምርና ቴክኖሎጅ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብደልሙህሲን ሀሰን ለሰልጣኞች ባስተላለፉት መልዕክት ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ዜጎችን ለከፋ እንግልትና ጉዳት እየዳረገ ለሀገርም ከፍተኛ ጫና እያሳደረ በመሆኑ ዘላቂ እልባት ለመፈለግ ለወጣቱ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫና ስልጠና መስጠት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡
 
ዶ/ር አብደልሙህሲን አክለዉም ሀገራችን በዉድድር ዓለም ላይ የምትገኝ በመሆኑ ወጣቱ ትዉልድ ከሱስና ከህገወጥ ስደት ተላቆ ሀገር ወዳድና ጤነኛ ትዉልድ ለማፍራት በየደረጃው ያሉ የአመራር አካላት ከማህበረሰቡ እና ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል ፡፡
 
በስልጠናዉ 45 የሚሆኑ ባለሙያዎች እየተሳተፉ የሚገኝ ሲሆን ለሁለት ቀናት እንሚቀጥል ተገልጧል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *