Assosa University

ለአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች የሕይወት ክህሎት ሥልጠና ተሰጠ

(አሶሳ ዩኒቨርሲቲ፣ የካቲት 15/ 2017 ዓ.ም) አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ለአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች በሕይወት ክህሎት፣ በኤች. አይ.ቪ እና በሥነ ተዋልዶ ጤና ዙሪያ ሥልጠና ሰጥቷል።

በሥልጠናዉ ላይ የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ሓላፊ መ/ር ንጋቱ ሀንቢሳ ተገኝተው ለሠልጣኝ ተማሪዎቹ መልዕክት አስተላልፈዋል። ተማሪዎች ለትምህርታቸው ብቻ ትኩረት በመስጠት ዉጤታማ እንዲሆኑ ሥልጠናዉ አስፈላጊ እንደሆነ ገልፀዋል። ጤናማ እና አምራች ትዉልድ ለሀገር እድገት ወሳኝ መሆኑን የጠቆሙት ጽ/ቤት ሓላፊዉ በጉዳዩ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ በተከታታይነት መሥጠት ያስፈልጋል ብሏል።

የሥልጠናው ዓላማ ተማሪዎች በሕይወታቸው ዉስጥ የሚያጋጥሟቸውን መሰናክሎች በብቃት በማለፍ በትምህርት ቆይታቸዉም ሆነ በሕይወት ዘመናቸዉ ጤናማ፣ ብቁ እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ እንደሆነ የገለፁት ደግሞ የዩኒቨርስቲዉ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈፃሚ መ/ርት መርቀኒያ አሊ ናቸዉ። ሥልጠናዉም ለ550 የአቅም ማሻሻያ ተጠቃሚ ተማሪዎች ለሁለት ቀናት እንደሚሰጥ ጭምር ሥራ አስፈፃሚዋ ጠቁመዋል።

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን

Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X

WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P

Facebook: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial

Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk

Email: pir@asu.edu.et

Instagram: https://www.instagram.com/asueduet/#

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *