Assosa University

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ለቅድመ ምረቃ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች የመዉጫ ፈተና እየተሰጠ ነዉ

(ጥር 27/2017 ዓ/ም) ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣዉ ፕሮግራም መሰረት ከጥር 26-30/2017 ዓ/ም በመደበኛ እና ቅዳሜና እሁድ ፕሮግራም ትምህርታቸዉን ሲከታተሉ የቆዩ የቅድመ ምረቃ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች የመዉጫ ፈተና በዩኒቨርሲቲዉ እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡
 
በዛሬዉ የፈተና ፕሮግራምም 190 የሚሆኑ የማናጅመንት ተማሪዎች የመዉጫ ፈተናዉን የወሰዱ ሲሆን በትምህርት ሚኒስቴር በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የፈተናዉ አስተባባሪ የሆኑት አቶ አድነዉ ኤርበሎ ፈተናዉ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በሰላም እየተሰጠ መሆኑን ገልፀዉ የመዉጫ ፈተናዉ በሰላም እንዲሰጥ ለሚተባበሩ የፀጥታ አካላት እና የዩኒቨርሲቲዉ ማህበረሰብ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
በወጣዉ የፈተና መርሃ-ግብር መሠረት በአጠቃላይ ከ2,122 በላይ ተማሪዎች በዩኒቨረሲቲዉ የመዉጫ ፈተና እንደሚወስዱ ታዉቋል፡፡
ተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *