Assosa University

ሴኔቱ የተለያዩ ዉሳኔዎችን አሳለፈ

ህዳር 03/2017 ዓ.ም
የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ዉሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
የዩኒቨርሲቲዉ ሴኔት የ2017 ዓ/ም የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች የትምህርት መርሃ ግብር (Academic Calendar) የመግቢያ ጊዜ ህዳር 16 እና 17/2017 ዓ/ም እንዲሆን እና የቅድመ እና ድህረ ምረቃ ተማሪዎችን ዉጤት ተወያይቶ አፅድቋል ፡፡
ከዚህ ተጨማሪም በማህበራዊ ሳይንስ እና ስነ ሰብ ኮሌጅ ሥር የነበረዉን የመልከአ ምድር መረጃ ሳይንስ (GIS) ትምህርት ክፍል ወደ ተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዝዉዉርን አጽድቋል።
እንድሁም በአባይ ተፋሰስ እና በህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚሰራ የምርምር ማዕከል ለማቋቋም የቀረበዉን ሰነድ ሴኔቱ ተወያይቶ አጽድቋል፡፡
በመጨረሻም አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በመስክ ልየታዉ የተግባር ተኮር (አፕላይድ ሳይንስ) ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የትኩረት መስኮቹንና የልህቀት ማዕከል ተግባራቶቹን የሚገልፅ የሪብራንድንግ እና የሎጎ መረጣ በማካሄድ ሥራ ላይ እንዲዉል ዉሳኔ ተላልፏል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *