Assosa University

ምሁራን በትምህርት ጥራት ላይ አተኩረዉ እንዲሰሩ ጥሪ ቀረበ

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ከትምህርቱ አመራር፣ ከተመራማሪዎች እና በዘርፉ ከሚመለከታቸዉ ባለ ድርሻ አካላት ጋር ጥራት ያለዉ ትምህርት ለማረጋገጥ የምሁራን ሚና ምን መሆን እንዳለበት ለመመካከር በተካሄደዉ ጉባኤ ለትምህርቱ ጥራት መሻሻል ሁሉም ባለድርሻ አካላት ትኩረት ሰጥተዉ እንድሰሩ ተገልጿል።
በጉባኤዉ ለመሳተፍ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሁሉም ዞኖች እና ከዩኒቨርሲቲዉ ለመጡ ተሳታፊዎች ዶ/ር አብደልሙህስን ሀሰን የዩኒቨርሲቲዉ የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዚዳንት በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸዉ ምሁራን በትምህርት ጥራት ማስጠበቅ ከፍተኛ ሚና ስላላቸዉ የድርሻቸዉን መወጣት እንዳለባቸዉ አሳስበዋል።
በተመሳሳይም የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ከማል አብዱራሂም ከተሰጡን ተልዕኮዎች ጎን ለጎን መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ከነደፋቸዉ ስትራቴጂዎች አንዱ የሆነዉን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሄራዊ ፈተናን ተማሪዎች ከኩረጃ በጸዳ መልኩ በራሳቸዉ ሠርተዉ በማለፍ ወደ ዩኒቨርሲቲ እንድገቡ የማድረጉን ተግባር ዩኒቨርሲቲዉ ዋና ተዋናይ ሆኖ እየሠራ መሆኑን በጉባኤዉ መክፈቻ ላይ ተናግረዋል።
በተጨማሪም ፕሬዚዳንቱ ያለ መምህራን አቅም የትምህርት ጥራት የማይመጣ በመሆኑ የሁለተኛ ደረጃ መምህራን እንዲሁም የቴክኒክ እና ሙያ አሰልጣኞችን ባሳለፍነዉ ክረምት በተቋማችን ገብተዉ የአቅም ግንባታ ስልጠና መዉሰዳቸዉ ለትምህርቱ ጥራት መጠበቅ ጉልህ ሚና ዩኒቨርሲቲዉ እየተጫወት መሆኑ አክለዉ ገልጸዋል።
በመድረኩ ላይም ዶ/ር አብደልሙህስን ሀሰን የቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል አጠቃላይ የትምህርት አፈጻጸምን የሚዳስስ ጥናታዊ ጽሁፍ በማቅረብ በትምህርት ጥራቱ የምሁራን ሚና ምን መሆን እንዳለበት በሳይንሳዊ ጥናት አስደግፈዉ አቅርበዋል።
በጉባኤዉ ላይ ጥናታዊ ጽሁፉን መነሻ በማድረግ ዉይይት የተካሄደ ሲሆን ዉይይቱንም የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ከማል አብዱራሂም እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ተመስገን ዲሳሳ መርተዉታል።
በዉይይቱም በሀገራችን መፍትሄ እየፈለገ የመጣዉን የትምህርት ጥራት ለማምጣት ምሁራን ሚናቸዉ ከፋተኛ መሆኑን በመስማማት በጥናት ላይ ተመስርቶ ክልላዊ የትምህርት ፖሊሲዉን በመቅረጽ እና በስርዓተ ትምህርት ዝግጅት ምሁራን ንቁ ተሳትፎ እንዳደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
በተጨማሪም የትምህርት አመራሩ በብቃት ላይ ተመስርቶ የድጋፍ እና ቁጥጥር ሥራዎችን መስራት ሲችል እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ክልል የገጠመንን የትምህርት ጥራት መጓደል መቅረፍ እንደሚቻል ጉባኤተኛዉ ተስማምቷል።
 
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *