Assosa University

ምሁራን ለትዉልድ ግንባታ የበኩላቸዉን ሚና መጫወት እንደሚገባ ተገለፀ።

(አሶሳ ዩኒቨርሲቲ፣ የካቲት 18/ 2017 ዓ.ም) ምሁራን ለትዉልድ ግንባታ ላይ የሚጠበቅባቸውን ሚና መጫወት እንደሚገባቸዉ ተገልጿል።

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ከኢፌዲሪ ሠላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ”ሀገራዊ ጥቅም እና ቀጠናዊ ትስስር ለሚዘናዊ የህዝብ ተጠቃሚነት” በሚል መሪ-ቃል የምሁራን የዉይይት መድረክ አዘጋጅቷል።

የዉይይት መድረኩ የተካሄደው በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የሠላምና የዉጭ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ አባል የተከበሩ ወ/ሮ ጥሩዓይነት ተመስገን እና የሠላም ሚኒስቴር ተወካይ አቶ ገዛኽኝ ጥላሁን በተገኙበት ሲሆን የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር አብዱልሙህስን ሀሰን ተገኝተዉ ንግግር አድርጓል። የሀገራዊ ጥቅሞቻችን ጉዳይ ለአምባሳደሮቻችን ብቻ የምንተወው ሥራ አለመሆኑን የጠቆሙት ዶ/ር አብዱልሙህስን ምሁራን በጥናት ላይ የተመሠረተ ቀጠናዊ ትስስር በሚፈጠርበት ሥራዎች ላይ ማገዝ እንዳለባቸዉ ገልፀዋል። ቀጠናዊ ትስስር ለእድገታችን ወሳኝ መሆኑን የገለፁት ምክትል ፕሬዚዳንቱ እንደ ዩኒቨርሲቲም አከባቢያዊ ትስስር ሊፈጥሩ በሚችሉ ጉዳዮች ትኩረት ሰጥተን እየተንቀሳቀስን ነዉ ብሏል።

በመድረኩ ቁልፍ መልዕክት ያስተላለፉት በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የሠላምና የውጭ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ አባል የተከበሩ ወ/ሮ ጥሩዓይነት ተመስገን ሲሆኑ ምሁራን በትዉልድ ግንባታ ላይ የሚጠበቅባቸዉ ሚና መጫወት እንዳለባቸው ገልፀዉ እንደ ሀገርም የጋራ መገለጫዎቻችን ላይ ትኩረት ሰጥተን ሠላማችን መጠበቅ አለብን ብለዋል። የሀገር ግዛት አንድነት እና ሚዛናዊ የህዝቦቻችን ተጠቃሚነት ላይ መደራደር የለብንም ያሉት የተከበሩ ወ/ሮ ጥሩዓይነት የጋራ እሴቶቻችን እና ከልዩነት ይልቅ አንድ በሚያደርጉን ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥተን መሥራት ይጠበቅብናል ብሏል።

በመቀጠልም “ብሔራዊ ጥቅሞቻችንና ቀጠናዊ ትስስር ለሚዛናዊ የህዝቦች ተጠቃሚነት” በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጽሑፍ በዩኒቨርሲቲዉ ህግ ትምህርት ቤት መምህርና ተመራማሪ መ/ር ኪዳኔ ደያሳ ቀርቦ ሰፊ ዉይይት ተደርጎበታል።

በዉይይት መድረኩ ላይ በርካታ ገንቢ ሀሳቦችና አስተያየቶች በስፋት የተነሱ ሲሆን በትዉልድ አቀራረጽ እና በተዛቡ ታሪኮቻችን ዙሪያ ሥራ መሥራት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል። መምህራንም ለዚህ ትልቅ ድርሻ ይኖራቸዋል ተብሏል። ሀገራችን ግጭት ዉስጥ ሆና እንኳን እያስመዘገበች ያላችሁ እድገት ሠላም ቢሆን ኖሮ ብዙ ርቀት መጓዝ ትችል ነበር ብሎ ቁጭታቸዉን ጭምር የገለፁት አስተያየት ሰጪዎቹ አሁንም የዉስጥ ሠላማችን በሚረጋገጥበት ጉዳዮች ላይ መሥራት አለብን ብሏል።

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን

Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X

WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P

Facebook: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial

Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk

Email: pir@asu.edu.et

Instagram: https://www.instagram.com/asueduet/#

 

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *