በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ STEM ማዕከል በዚህ ክረምት 300 ተማሪዎች ከቤንሻንጉል ጉሙዝ 2ኛ ደርጃ ትምህርት ቤቶች የተመደቡ ሲሆን የማጠናክሪያ ተምህርቱን ለመሥጠት አቀባበልና ስለሚኖራቸዉ ቆይታ ገልፃ ተደርጎላቸዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር (ዶ/ር) ተፈራ ተሸመ ሲሆኑ ዩኒቨርሲቲዉ የ2017 ዓ.ም ለክረምት መርሃ ግብር ስቴም ስልጠና ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማሰልጠን በክልሉ ከሚገኙ ሦስቱ ዞኖችና ከማኦና ኮሞ ልዩ ወረዳ ትምህርት ቤቶች ከ9-11ኛ ክፍል የተወጣጡ የሳይንስ ዝንባሌ ያላቸውን ሰልጣኝ ተማሪዎች ተቀብሎ በሳይንስና ቴክኖሎጂ መስኮች ያላቸውን ዕውቀት በተግባር በተደገፈ መልኩ እንዲያዳብሩ የተዘጋጀ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡
አክለውም ተማሪዎች ወደፊት ለሀገር እና ለወገን የሚጠቅም የፈጠራ ስራን ለመስራት ዛሬ ላይ ይህን ዕድል ተጠቅመው ስልጠናውን በአግባቡ መከታተል እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡ ለሰልጣኞችም መልካም የስልጠናና የትምህርት ጊዜ እንዲሆንላቸው ምኞታቸውን ገልጸዋል።
የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ዲን ጽ/ቤት ሃላፊ መ/ር ጌታቸዉ ገለታ በበኩላቸው፤ ለክረምት ስልጠና የመጡ STEM ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው የምግብ፣ የህክምና እና የመኝታ አገልግሎት እንደተመቻቸላቸው ገልጸው፤ ተማሪዎች በሚኖራቸው ቆይታ የተቋሙን ሀብትና ንብረት በአግባቡ መያዝና መጠበቅ እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል።
በዩኒቨርሲቲ STEM ማዕከል በክረምት መርሐ ግብር የሚሰለጥኑ ከ300 በላይ ሰልጣኝ ተማሪዎች ለተከታታይ 45 ቀናት ስልጠናውን የሚወስዱ መሆኑ ለማወቅ ተችሏል።
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et
Instagram: https://www.instagram.com/asueduet/#