በአሶሳ ዪኒቨርሲቲ ሴቶች ጉዳይ አካትቶ ትግበራ ሥራ አስፈፃሚ አዘጋጅነት ለአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial) ተማሪዎችበህይወት ክህሎትና በአደንዛዥ ዕፅ አስከፊነት ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
በስልጠናው ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሴቶች ጉዳይ አካትቶ ሦራ አስፈፃሚ የሆኑት መ/ርት መርቀኒያ አሊ ሲሆኑ ዪኒቨርሲቲ አዲስ አካባቢን፥ ጓደኛን እና ነፃነትን የምናገኝበት በመሆኑ ይህ ነፃነት ትልቅ ኃላፊነትን ይዞ የሚመጣ ስለሆነ የተገኘውን ዕድል በአግባቡ መጠቀም እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
የዪኒቨርሲቲ ቆይታችሁ የታሪካችሁ አድስ ምዕራፍ በመሆኑ ህይወታችሁ በእውቀትና በስኬት እንዲጠናቀቅ ዛሬ ላይ የምትመርጡት ምርጫ ወሳኝ ሚና አለውና ራሳችሁን ከአደንዛዥ ዕፅ በመጠበቅ እና ክህሎታችሁን በማዳር ለመጣችሁበትን አላማ በማሳካት ለራስ፥ ለማህበረሰብ እና ለሐገር የሚጠቅም ዕውቀት ይዞ መውጣት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
በተጨማሪም የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት የሆኑት ተመሪ መልካሙ ተገኝተው ተማሪዎች በዪኒቨርሲቲ ቆይታቸው ሊተገብሯቸው የሚገቡ ጉዳዮችን አስረድተው የዩኒቨርሲቲ መልካም ተሞክሯቸውን አካፍለዋል።
በስልጠናው ራስን ማወቅ፥ ውሳኔ አሰጣጥ፥ የጊዜ አጠቃቀም፥ አቻ ግፊት መቋቋም እና አደንዛዥ ዕፅ አስከፊነት ዙሪያ በመ/ርት ኤልሳቤት ተመስጌን እና በመ/ር ሀይማኖት ታረቀኝ ተሰጥቷል።
ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ገፆቻችን ይከተሉ
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Website: www.asu.edu.et
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et




