Assosa University

ለዩኒቨርሲቲዉ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ክበብ አባላት ስልጠና ተሰጠ

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ለነባርና አዲስ ለተመዘገቡ የሥነ-ምግባርና ፀረ- ሙስና ክበብ አባላት በአደረጃጀት የአሰራር መመሪያ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ፡፡

የዩኒቨርሲቲዉ ተማሪዎች በትክክለኛ ስነ-ምግባር ለእዉቀት የሚሰሩና የሚኖሩ፣በሰሩትና በለፉት ለመክበር የሚተጉ ሆነዉ እንዲወጡ የሥነ- ምግባር ግንባታ ላይ መስራት እንደሚያስፈልግ ስልጠናዉን የሰጡት የሥነ ምግባር መከታተያ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ያየህራድ አጥናፉ ተናግረዋል፡፡

አቶ ያየህራድ አጥናፉ አክለዉም ተማሪዎች ከግቢዉ ማህበረሰብ ጋር የሚኖራቸዉን ግንኙነት በመልካም ሥነ-ምግባር እሴቶች ላይ የተመሰረተ በማድረግ የመጣችሁበትን ዓላማ በማሳካት ቤተሰባችሁን እና ሀገራችሁን የሚጠቅም ስራ መስራት አለባችሁ ሲሉ አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻም በዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ኃላፊ በሆኑት በመ/ር ንጋቱ አምቢሳ አስመራጭነት በቀጣይ ክበቡን የሚመሩ ሰባት የአደረጃጀት ሥራ አስፈፃሚ አባላት  ተመርጠዋል፡

 

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን

Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X

WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P

Facebook: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial

Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk

Email: pir@asu.edu.et

Instagram: https://www.instagram.com/asueduet/#

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *