ህዳር 05/ 2017 ዓ.ም
በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎች መኝታ ቤት ተቆጣጣሪዎች እና ምግብ ቤት ሰራተኞች በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ያተኮረ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
ስልጠናውን የከፈቱት የተማሪዎች ስብዕና ግንባታ ም/ዲን መምህርት መቅደስ ደርቤ ሲሆኑ
የስልጠናውን ዓላማ ሲያብራሩ ሰልጣኞች ለተገልጋዮች ነፃ፣ ገለልተኛ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጥ እንዲችሉ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማድረግ መሆኑን ገልጸዋል።
ስልጠናዉ አዘዉትረዉ ከተገልጋዮች ጋር ለሚገናኙ የዩኒቨርሲቲዉ አገልግሎት ሰጭ ሰራተኞች የተዘጋጀ ስልጠና ሲሆን ከህዳር 04/2017 ዓ/ም ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ለ420 የተማሪዎች መኝታ ቤት ተቆጣጣሪዎች እና ምግብ ቤት ሰራተኞች ተሰጥቷል፡፡
ይህ ስልጠና በዩኒቨርሲቲዉ ስትራቴጅክ ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ በሆኑት በአቶ ታከለ መኮንን የተሰጠ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ የአቅም ማሻሻያ እና የማነቃቂያ ስልጠናዎችን ለሰራተኞች ሲሰጥ የነበረ መሆኑ ይታወሳል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et
Instagram: https://www.instagram.com/asueduet/#