Assosa University

ለዩኒቨርሲቲዉ አመራሮች በሳይንስና ቴክኖሎጅ ፈጠራ ፖሊሲ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

የፌደራል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለዩኒቨርሲቲው አመራሮች በሳይንስና ቴክኖሎጅ ፈጠራ (Science and Technology Innovation) ፖሊሲ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
 
በስልጠናዉ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የምርምርና ቴክኖሎጅ ሽግግር ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር አብዱልሙህሰን ሀሰን ሀገራችን በቴክኖሎጅና ፈጠራ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ ገልፀዉ በዩኒቨርሲቲዉ ምሁራን የሚሰሩ ምርምሮችና የፈጠራ ስራዎችን ከኢንዱስትሪው ጋር በማገናኘት የአካባቢዉን ማህበረሰብ እና የሀገር ልማትን ማሳደግ የሚችሉ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
 
ስልጠናው ዋና አላማ፣ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር ተሻሽሎ የፀደቀውን የሳይንስና ቴክኖሎጅ ፈጠራ ፖሊሲ ላይ የዩኒቨርሲቲውን አመራሮች ግንዛቤ በማሳደግ፣ ብቁ የሰው ሀይል መፍጠር፣ በሳይንስና ቴክኖሎጅ፣ ምርምር እና ፈጠራ ስራዎችን ማሳደግ፣ ከግል ዘርፉ ጋር በጋራ መስራት እና የሀገር በቀል ዕውቀቶችን በማልማት ጥቅም ላይ ማዋል እንዲቻል ለማድረግ ነው።
 
በስልጠናው የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች፣ ስራ አስፈፃሚዎች፣ ቡድን መሪዎችና አስተባባሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ስልጠናው ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር በመጡ በዶ/ር አበበ ሞላ እና በዶ/ር በኩረፅዮን አለማየሁ ተሰጥቷል።
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *