በዩኒቨርሲቲዉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈፃሚ አስተባባሪነት የተዘጋጀው የህይወት ክህሎት ስልጠና ለሁለት ተከታታይ ቀናት ይስጣል።
በሥልጠናዉ ላይ ተገኝተዉ መልዕክት ያስተላለፉት የዩኒቨርሲቲዉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈፃሚ መ/ርት መርቀኒያ አሊ ሲሆኑ የሥልጠናዉ ዓለማ ወደ ዩኒቨርሲቲዉ የሚገቡ ተማሪዎች በዕዉቀትና በክህሎት ላይ የተመሠረቱ ዉሳኔዎችን የመወሰን ብቃት በማዳበር በህይወታቸዉ ዉስጥ የሚገጥማቸዉን ፈተናዎች ወደ መልካም አጋጣሚዎች በመቀየር ለዉጤት እንዲበቁ ታስቦ የተዘጋጀ ስለመሆኑ አስረድተዋል፡፡
መ/ርት መርቀኒያ አክለውም ለተማሪዎች ቀጣይነት ባለው መልኩ በዋናነት ሴት እህቶችን ከፆታዊ ጥቃት ራሳቸዉን እንዲከላከሉ ከኤቺ. አይ.ቪ ና መሰል በሽታዎች ራሳቸዉን እንዲጠብቁ ምክራቸዉን ለግሰዋል።
በተጨማሪም በመማር ማስተማሩ ሂደት እርስ በርስ እንዲደጋገፉና በተለይም ሴቶችና አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን በተሳሳቱ አመለካከቶች ከትምህርታቸዉ እንዳይስተጓጉሉ ትኩረት ተሰጥቶ የመደገፍ ሥራ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራ ስለመሆኑ ገልፀዋል፡:
በተመሳሳይ መልኩ የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ መምህር ንጋቱ ሀቢሳ በበኩላቸው የህይወት ክህሎት ሰዎች በዕለት ተዕለት ኑሯቸዉ የሚያስፈልጋቸዉን ለማሟላትና የሚያጋጥሙአቸዉን ፈተና ለመሻገርና ለመፍታት የሚጠቀሙበት ክህሎት መሆኑን ገልጸዋል። የጽ/ቤቱ ሀላፊ ከዚህ ጋር አያይዘዉም ተማሪዎች በራስ የመተማመን ክህሎትን፣ የአቻ ግፊትን መቋቋምን እና ዉሳኔ የመስጠትን ችግሮችለመፍታትእንዲችሉ ለማስቻል ስልጠናዉ እንደሚያግዝ ገልጸዋል።
በተጨማሪም የትምህርት ክህሎታቸዉን ለማዳበር እና በኤች.አይ.ቪ እንዲሁም በስነ-ተዋልዶ ጤና ያላቸዉን ግንዛቤ በማስፋት በህይወታቸው ውጤታማ ለመሆን ስልጠናውን ትኩረት በመስጠት እንዲከታተሉ አሳስበዋል።
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et
Instagram: https://www.instagram.com/asueduet/#