Assosa University

ለአንደኛ ዓመት ተማሪዎች የትምህርት ክፍል መረጣ ገለጻ ተደረገላቸዉ

በዘንድሮዉ ዓመት በአንደኛዉ ወሰነ ትምህርት ትምህርታቸዉን ተከታትለዉ ላጠናቀቁ ተማሪዎች በሁለተኛዉ ወሰነ ትምህርት የትምህርት ክፍል መረጣ በማድረግ ትምህርታቸዉን እንድከታተሉ ለማስቻል በዛሬዉ እለት ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ገለጻና ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
 
ገለጻና ማብራሪያዉን የሠጡት የዋናዉ ሬጅስትራር ዳይሬክተር ደ/ር ሀብታሙ ሸንቁጥ፣የአካዳሚክ ፕሮራሞች ዳይሬክተር ዶ/ር ወንድም መኩሪያዉ እንዲሁም የኢንጂነሪንግና ኮምፒዉቲንግና ኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ ዲኖች ሲሆኑ የኮሌጅና የትምህርት ክፍል ምርጫዉ ዉጤትን እና ፍላጎትን መሰረት ያደረገ መሆኑን ገልጸዉ ለኮሌጅ መረጣ መወዳደሪያ የሚሆነዉን የመግቢያ ፈተና በነገዉ ዕለት እንደሚሰጥ ተነግሯል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *