ህዳር 20/2017 ዓ.ም
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም ትምህርት ዘመን አዲስ ለተመደቡ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች በቆይታቸዉ ዉጤታማ ስለሚያደርጓቸዉ ጉዳዮች ገለፃ እና ማብራሪያ በዛሬዉ ዕለት አድርጎላቸዋል።
በፕሮግራሙ ላይ የካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር መልካሙ ደሬሳ እና የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጌታቸዉ ዓለሙ ተገኝቸዉ ለተማሪዎቹ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በአካዳሚክም ሆነ በአስተዳደርና ልማት ዘርፎች ለተማሪዎቹ የሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ ያተኮረ ጥልቅ ገለፃ በሚመለከታቸዉ የሥራ ክፍል ሀላፊዎች ተሰጥቷል።
በመማር ማስተማሪ ዙሪያ በተማሪዎች ኦንላይን ምዝገባ አተገባበር፣ በe-learning፣ በትምህርት ጥራት እና በሥነ ምግባር ዙሪያ ገለፃ ተደርጎ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ተከናዉኗል።
በተመሳሳይም በአስተዳደር በኩል የመኝታ ቤት፣የምግብ ቤት እና የክሊኒክ አገልግሎቶች አሰጣጥ ህግና ስርዓት ተከትለዉ መገልገል እንደሚገባ እና እንዴት መጠቀም እንዳለባቸዉ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
በመጨረሻም በተደረገዉ ዉይይት ላይ ተማሪዎቹ መስተካከል የሚገባቸዉን አስተያየቶችና መልስ የሚፈልጉ ጉዳዮችን አንስተዉ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et
Instagram: https://www.instagram.com/asueduet/#