Assosa University

ለአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዉ ስለሚኖራቸዉ ቆይታ ገለፃ ተደረገላቸዉ

(አሶሳ ዩኒቨርሲቲ፣ ጥር 27/ 2017 ዓ.ም) አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ለ2017 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዉ ስለሚኖራቸዉ ቆይታ ገለፃ አድርጎላቸዋል።
 
በፕሮግራሙ ላይ የሬጂስትራር አገልግሎት ዳይሬክተር ዶ/ር ሀብታሙ ሽንቁጥ የካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንትን ወክለዉ ለተማሪዎቹ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ዩኒቨርሲቲዉ በ2016 ዓ.ም በአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ ባደረገዉ ርብርብ ከ96% በላይ ጥሩ ዉጤት በማስመዝገብ ወደ 1ኛ ዓመት ማለፋቸዉን ገልፀዋል።
 
ዘንድሮም ከዚህ ለበለጠ ዉጤት በትኩረት እንደሚሠራ ተናግረዉ ለዚህም ተማሪዎች ለመጡለት ዓላማ ብቻ በማትኮር ዉድ ጊዜያቸዉን በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባቸዉ አጽንኦት ሰጥቷል።
 
በመቀጠልም በዩኒቨርሲቲዉ ታሪካዊ ዳራ፣ በተማሪዎች መብትና ግዴታ እንዲሁም የሚሰጡ አገልግሎቶች ዙሪያ በሚመለከታቸዉ የሥራ ሓላፊዎች እና ባለሙያዎች ለተማሪዎቹ ሰፊ ገለፃ ተደርጎላቸዉ ለግንዛቤ ዉሏል።
ተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *