Assosa University

ለተቋምና ትምህርት ፕሮግራሞች እዉቅና አሰጣጥ ሥልጣና ተሰጠ

ህዳር 04/ 2017 ዓ.ም
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ለተቋምና ትምህርት ፕሮግራሞች እዉቅና አሰጣጥ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጣና ሰጥቷል፡፡
ሥልጠናዉ ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ተቋማትና ፕሮግራሞቻቸዉ እዉቅና የሚያገኙበት ሂደቶችና ማሟላት ያለባቸዉን መስፈርቶች ላይ ግንዛቤ ተፈጥሮ ወደ ሥራ እንዲገቡ ባስቀመጠዉ አቅጣጫ መሠረት ዩኒቨርሲቲዉ ለትምህርት ክፍል ኃላፊዎች፣ ዳይሬክተሮች፣ ኦፍሰሮችና ለሥራ አስፈጻሚዎች ሥልጠና ሰጥቷል፡፡
ሥልጠናዉን ያስጀመሩት የዩኒቨርሲቲዉ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር መልካሙ ዴረሳ በሀገርም ሆነ ዓለም አቀፍ ደረጃ ብቁ እና ተወዳዳሪ ምሩቃንን ለማፍራት ለትምህርት ጥራት ትኩረት መስጠት እጅግ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዉ ለዚህም እዉቅና ያላቸዉ የትምህርት ፕሮግራሞች እንዲኖሩን መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በቀጣይነት የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራዉም ለሁሉም መምህራን ጭምር ተደራሽ እንደሚሆን ገልፀዋል፡፡ በትግበራዉም ሂደት የሚታዩ ዉስንነቶች እያስተካከልን ከወዲሁ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ሥልጠናዉ በአካዳሚክ ፕሮግራሞች ዳይሬክተር በዶ/ር ወንድም መኩሪያ እና የትምህርት ጥራት ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በዶ/ር ገለታ ፍቃዱ ተሰጥቷል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *