Assosa University

ለምርምር ማዕከሉ ለቀረቡ የምርምር ትልሞች ግምገማ እየተካሄደ ነዉ

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ለትሮፕካል እና ተላላፊ በሽታዎች ምርምር ማዕከል ለቀረቡ የምርምር ትልሞች (ፕሮፖዛል) ግምገማ እያካሄደ ይገኛል።

የምርምር ፕሮፖዛል ግምገማዉ የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚደንት ዶ/ር ዑመር ሸሪፍ በይፋ ያስጀመሩ ሲሆን ለዚሁ ማዕከል ምርምር ሥራ የቀረቡት 6 የምርምር ትልሞች በወጣላቸዉ መገምገሚያ መስፈርት መሠረት ታይቶ ያለፉ ወደ ምርምር ሥራ እንደሚገቡ ገልፀዋል።

ግምገማዉ በዩኒቨርሲቲዉ የምርምር ማዕከላት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሓላፊ ዶ/ር ቱጌ ተመስገን የሚመራ ሲሆን ተሳታፊዎቹም የፕሮፖዛል አቅራቢዎችና የሚመለከታቸው መምህራን ናቸዉ።

ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ገፆቻችን ይከተሉ

Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X

Website: www.asu.edu.et

WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P

Facebook: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial

Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk

Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *