አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ከጅረት ሠላምና ዕርቅ ድርጅት ጋር የትብብር ሰነድ ተፈራረመ
ጥቅምት 26/2017ዓ.ም
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ከጅረት ሠላምና ዕርቅ ድርጅት ጋር በአሶሳ ዞን በባምባሲ ወረዳ በዘላቂ ሠላም ግንባታ ዙሪያ በትብብር ለመስራት የሚያስችለዉን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡
ጅረት የሠላምና እርቅ በሠላም ላይ አተኩሮ የሚሠራ መንግስታዊ ያልሆነ ዓለም አቀፋዊ ድርጅት ነዉ።
የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጅ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት አብዱልሙህስን ሀሰን (ዶ/ር) በስምምነት ፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ ዩኒቨርሲቲዉ ከበርካታ ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ እንደሚገኝ አዉስተዉ በክልሉ የሚኖረዉ ማህበረሰብ በሠላም አብሮ መኖር እንዲችል በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የጅረት ሰላምና ዕርቅ ድርጅት ሀላፊ አቶ ዳዊት ሀይሌ በበኩላቸዉ ድርጅቱ የፀጥታ ችግር በሚስተዋልባቸዉ አካባቢዎች በዕርቅ ዘላቂ ሠላም ማምጣት ላይ እንደሚሰራ ገልፀዉ ተቋማቸዉ ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ለመስራት በመፈራረሙ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በስምምነቱ መሰረት የሁለቱ ተቋማት ትብብር በወረዳዉ ለሚኖረዉ ማህበረሰብ ፍቃደኞችን ለማህበረስብ እድገት ማሰማራት፣ የግጭት አፈታት እና ዘላቂ ሠላም ግንባታ ላይ በመስራት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሕይወት ማሻሻል ላይ ያተኩራል ተብሏል፡፡
ስምምነቱን የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጅ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ዶክተር አብዱልሙህስን ሀሰን እና የጅረት ሠላምና ዕርቅ ሀላፊ አቶ ዳዊት ሀይሌ ተፈራርመዋል።
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et
Instagram: https://www.instagram.com/asueduet/#