በዩኒቨርሲቲው የሥራ ፈጠራና ባህል ማዕከል ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ለቲያትርና ስነጽሁፍ ክለብ አባላት በመሰረታዊ የስነ-ጽሑፍና ተውኔት ዙሪያ ከታህሳስ18/2014 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት ሲሰጥ የነበረው ሥልጠና ተጠናቋል። የስልጠናው አላማም አባላቱ ሙያን መሰረት ያደረገ የኪነ ጥበብ ሥራዎችን በመስራት ለዩኒቨርሲቲው እና ለአካባቢው ማህበረሰብ የሚሰጠውን አገልግሎት ባህሉን ፣ ወጉን እና ትውፊቱን የጠበቀ በማድረግ እያዝናኑ ማህበረሰቡን ማስተማር እንዲችሉ ለማስቻል የተዘጋጀ ሥልጠና መሆኑ የቲያትር ክፍል ዝግጅት አስተባባሪ የሆኑት አቶ አለሙ ሊቁ ገልፀዋል።