Assosa University

ዩኒቨርሲቲዉ ባሕላዊ ህክምናን ለማጠናከር እየሰራ መሆኑን ገለፀ

ዩኒቨርሲቲዉ ከቤ.ጉ.ክ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር “የቤጉ ህዳሴ ባህላዊ ህክምና አዋቂዎች ማህበር” በማቋቋም በህክምናው ዘርፍ የበኩላቸዉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ለማስቻል እየተንቀሳቀሰ ሲሆን ይህንንም ሥራ ለማጠናከር ከባለድርሻ አካላት ጋር የዉይይት መድረክ አዘጋጅቷል።
 
በዉይይት መድረኩ የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ሕትመት ሥነ ምግባር ሥርፀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ዑመር ሸሪፍ ተገኝተዉ መልዕክት አስተላልፈዋል። ባህላዊ ህክምና በብዙ ሀገራት አገልግሎት ላይ እንደሚዉል የጠቀሱት ዶ/ር ዑመር በሀገራችን ኢትዮጵያም ከ80% ያላነሰ የህዝብ ቁጥር እንደሚገለገልበት ጥናቶች ያሳያሉ ብላል።
እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ ከዋጋ እና አቅርቦት አንፃር ከዘመናዊ ይልቅ ባህላዊ ህክምና በህብረተሰቡ ዘንድ ተመራጭ ቢሆንም በዘርፉ በርካታ ተግዳሮቶች መኖራቸዉን አብራርተዋል። የህግና የፖሊሲ ክፍተቶች፣ የመማርና የሥልጠና እጥረት፣ የተዛቡ የማህበረሰብ እይታ፣ የፋይናንስ ዉስንነት፣ የባህላዊ መድሃኒት አቅርቦትና የዘመናዊ መሳሪያዎች እጥረት እንዲሁም ወጥ የሆኑ ባህላዊ ህክምና አለመኖር የጥራት ማረጋገጫ የዘርፉ ማነቆ መሆናቸዉን ዳይሬክተሩ ገልፀዉ ለዚህም ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ ባለድርሻዎች ችግሮቹ በሚቀረፉበት ላይ መሥራት ይጠይቃል ብሏል።
 
የምክክር መድረኩ ዓላማም የተቋቋመዉ የቤጉ ህዳሴ የባህል ህክምና አዋቂዎች ማህበር በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ ለመሥራት መሆኑን ጭምር ገልፀዋል።
በመድረኩ የክልሉ ጤና ቢሮ የክሊኒካል ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ሉቁማን አሊ፣ የማህበሩ ሰብሳቢ አቶ አብዱልጀባር በድሩ እና የሚመለከታቸዉ የዘርፉ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት እንዲሁም የባህል ህክምና አዋቂዎች ተሳትፈዋል።
 
በባህላዊ ህክምና ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮች እና በቀጣይ የሚከናወኑ ተግባራት ላይ ሰፊ ዉይይት ተካሂዷል።
በዩኒቨርሲቲዉ ሀገር በቀል እዉቀት ኦፍሰር ሥራ ክፍል በክልሉ በሚገኙ የሀገር በቀል እዉቀቶችን በማጥናት፣ በማደራጀትና በመሰነድ ልማት ላይ እንዲዉሉ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን የገለፁት ደግሞ የሀገር በቀል እዉቀት ኦፍሰር ዶ/ር አልማዝ ደቼ ናቸዉ።
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *