Assosa University

የፓርላማ አባላት ጉብኝት እንደቀጠለ ነው

ጥቅምት 26/2017ዓ.ም

የሰው ሀብት ልማት ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በዩኒቨርስቲው የሚያደርጉትን ጉብኝት ቀጥሎ ውሏል።
በዩኒቨርስቲው ፕሬዝደንት በተመራው በዕለቱ ጉብኝት የተጠናቀቁ እና በግንባታ ላይ ያሉ የግንባታ ፕሮጀክቶችን የተማሪ አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን እና መሰረተ ልማቶችን ተመልክተዋል።
ኮሚቴው ከሰዓት በኋላ በነበረው ቆይታ በተናጥል ከመምህራን ከሰራተኞችና ከተማሪዎች ጋር በአጠቃላይ የዩኒቨርስቲው መስተጋብር ላይ ጥልቅ ውይይት የአካሄዱ ሲሆን ከመምህራን ጋር የተካሄደውን ውይይት የመሩት የተከበሩ ዶክተር ቤቴልሄም ላቀዉ “ዩኒቨርሲቲው ያሉበትን ጫና ተቋቁሞ እየሰራ መገኘቱ ሊያስመሰግነው ይገባል ብለዋል።”
መምህራንና ሰራተኞች በበኩላቸው ሠራተኛው በሙሉ አቅሙ እንዳይንቀሳቀስ የመኖሪያ ቤት መስሪያ አለማግኘት የእርከን ጭማሪ ያለ መኖር እና ከኤሌክትሮኒክ ግዥ ጋር ተያይዞ የግብዓቶች መሟላት መጓተትን እንደዋና ችግር አንስተው ቋሚ ኮሚቴው ከባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት ችግሮችን እንዲፈቱ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
የኮሚቴ አባላቱ ክትትልና ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ እና የተጠቀሱት ችግሮች እንዲፈቱ ጥረት እንደሚያደርጉ በስብሰባው ማጠቃለያ ላይ ተናግረዋል።
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X

WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P

Facebook: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial

Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk

Instagram: https://www.instagram.com/asueduet/#

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *