Assosa University

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ከ IRC ጋር በመተባበር ተፈናቃዮች በሚኖሩበት አካባቢ የሚደርሰዉን ተጽእኖ ለማጥናት የጀመረዉን ሂደት ገምግሟል

ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም
በዛሬዉ ዕለት IRC ባዘጋጀዉ መድረክ ላይ በዩኒቨርሲቲዉ የተፈናቃዮች ተጽእኖን(displacement affected community)ጥናት ለመስራት በዩኒቨርሲቲዉ የተቋቋመዉ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር አብደል ሙህስን ሀሰን፣የአሶሳ ከተማ አስተዳደር በጥናቱ ላይ የሚሳተፉ አካላትና ሌሎች መንግስታዊ ያልሆኑ አጋር አካላቶች በተገኙበት በጥናቱ ሂደት ላይ ዉይይት አካሂደዋል፡፡
ዶ/ር አብደል ሙህስንም በዩኒቨርሲቲዉ የተቋቋመዉ የጥናት ቡድን ጥናቱን የሚከናዉንበትን የጊዜ መርሃ ግብር(Schedule) ያቀረቡ ሲሆን በተጨማሪም የጥናቱ ስራ ሂደት ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ በአሁኑ ሰዓት ላይ  ከዩኒቨርሲቲዉ እና ከከተማ አስተዳደሩ በጋራ በመሆን 40 የመረጃ ሰብሳቢዎች ተሳትፈዉ መረጃዉ በትንተና ሂደት ላይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የጥናቱ ዉጤትም በተመሳሳይ መድረኮች እየተገመገመ  በወጣለት የጊዜ መርሃ ግብር መሰረት  በያዝነዉ ዓመት የካቲት ወር መጨረሻ ላይ ጥናቱ ተጠናቆ ጥናቱን ለሚያሰራዉ IRC ማስረከብ እንደሚቻል አስረድተዋል፡፡
በዉይይቱ ላይ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላትም ዩኒቨርሲቲዉ ይህንን ጥናት በማጥናት በማህበረሰቡ ላይ ተፈናቃዮች የሚያደርሱትን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽእኖዎች ሳይንሳዊ በሆነ ጥናት በማስደገፍ ለአጋር ድርጅቶች በማስረዳት የከተማዉ ማህበረሰብ ችግሮች እንድፈቱ መስራቱን አመስግነዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *