አሶሳ ዩኒቨርሲቲ  ከአስር የክልል ሴክተር  መስሪያቤቶች  ጋር  የጋራ የመግባቢያ ሰነድ  ተፈራረመ

ዩኒቨርሲቲው ሰኔ 15/2ዐዐ9 ዓ/ም ከክልሉ ሴክተር መስሪያቤቶች ጋር በጋራ ለመስራት እንዲችል የውል ስምምነት / Memorandum of understanding/ ተፈራርሟል፡፡

 

በበጀት ዓመቱ ጥሩ የስራ አፈፃፀም ስመዘገቡ ሰራተኞች እውቅና ተሰጠ

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በ22/11/ዐ9 ዓ.ም በ2ዐዐ9 የበጀት ዓመት ጥሩ የስራ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የአስተዳደር ሰራተኞች ፣ መምህራን ፣ የት/ት ክፍል ሀላፊዎች ፣ አስተባባሪዎች ፣ ቡድን መሪዎች እና መካከለኛ አመራሮች የምስክር ወረቀትና የገንዘብ ሽልማት አበረከተ፡፡

ያንብቡት…

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በክልሉ ለሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የማጠናከሪያ ት/ት በመስጠት ላይይገኛል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በሀምሌ ወር 2ዐዐ8 ዓ.ም በሶስቱም ዞኖች ለተውጣጡ በክልሉ የሚገኙ ተማሪዎችን ከክልል ት/ት ቢሮ ጋር በመሆን ምልመላውን ካደረገ በ|ላ ትምህርቱን በመስጠት ነበር ይህን የክረምት የመጠናከሪያ ፕሮግራም የጀመረው፡፡

ያንብቡት…

FH ኢትዮጵያ ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳለዉገለፀ

ሀምሌ 29/2ዐዐ9 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፤የግብርናና የተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ መምህራን፣ የአልሙናይ ኢንዱስትሪ ትስስር እና የፋርም ዳይሬክቶሬቶች እና ባለሙያዎች በተገኙበት በባምባሲ ወረዳ ባሉ ሁለት ቀበሌዎች ላይ FH ኢትዮጵያ በሰጣቸዉ ስልጠና መሰረት የቁጥብ እርሻ ልማትን ተገባራዊ ያደረጉ አርሶ አደሮች ማሳ ጉብኝት አድርጓል፡፡ 

ያንብቡት…

The Universiyty Provides Deliverology Training for all Level Leaders
The Universiyty provided one day training for the presidents, College Deans , directors ,coordinators and department heads on August 15/2009 E.C. The objective of the training was to introduce the new concept of deliverology, higher education targets on deliverology as well as what is planning in deliverology and how it implements.
read more...

Assosa University’s Bamboo seedling plantation

The month of August is the commemorating month of the late Prime Minister Meles Zenawi death in the country level.

የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ ዋና ዋና ተግባራት

የፕሬዚዳንቱ የቅርብ አማካሪና ረዳት ሆኖ ይሠራል፣ የፕሬዚዳንት ጽ/ቤትን የሥራ እንቅስቃሴ በበላይነት ይመራል፣ የጽ/ቤቱን ጉዳዮች ከፋካልቲዎች፣ የአስተዳደር ክፍሎች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተገናኘ ያስፈጽማል፡፡

ዝርዝር ተግባራት

 1. የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ከፕሬዚዳንቱ በሚሰጠው መመሪያ መሠረት ይመራል፡፡
 2. የፕሬዚዳንቱ  የቅርብ ረዳት በመሆን ያማክራል፡፡
 3. ለፕሬዚዳንት ጽ/ቤት የሚጻፉ ደብዳቤዎችን፣ ሪፖርቶችን፣ ማስታወሻዎችን፣ መግለጫዎችን፣ ፕሮፖዛሎችን ወዘተ … በመመርመር ፕሬዚዳንቱ ውሳኔ ከሚሰጡበት በስተቀር ሌሎች ማስታወሻዎችን በማያያዝ ለሚመለከታቸው ፋካልቲዎች፣ የሥራ ሂደቶችና ሌሎች የሥራ ክፍሎች ይመራል፡፡
 4. የተለያዩ ጉዳችን ለማስፈፀም ከም/ፕሬዚዳንቶች፣ ከዲኖች፣ ከሥራ ሂደት መሪዎችና ሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቀጥታ እየተገናኘ አስፈላጊውን ክትትል ያደርጋል፡፡
 5. ለፕሬዚዳንቱ በቀጥታ የሚፃፉም ሆነ በፕሬዚዳንቱ መታየት የሚገባቸውን ጉዮች እንደየሁኔታቸው ማስታወሻ እያዘጋጀ ያስወስናል፣ በቀጥታ መልስ የሚሰጥባቸውን ደብዳቤዎች ለይቶ ተገቢውን መልስ ያዘጋጃል፡፡
 6. በየጊዜው ለዩኒቨርሲቲው የሚላኩ አዋጆችን፣ መመሪያዎችን፣ ደንቦችን ለሚመለከታቸው አካላት እንዲደርሱ ያደርጋል አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፡፡
 7. በፕሬዚዳንቱ፣ በአስተዳደር ካውንስሉ፣ በዩኒቨርሲቲው ቦርድ የሚተላለፉ ውሳኔዎችን ለሚመለከታቸው እንዲደርሱ ያደርጋል፡፡ ስለመፈፀማቸው ይከታተላል፣ ውሳኔ ስላላገኙ ጉዳዮች ምክንያታቸውን በመዘርዘር ለፕሬዚዳንቱ ያሳውቃል፡፡
 8. የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ደንበኞችን፣ አጋር አካላትን ሆነ እንግዶችን ተቀብሎ ያነጋግራል፣ ተገቢውን መልስ ይሰጣል፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ፕሬዚዳንቱን እንዲያገኙ ፕሮግራም ይይዛል፡፡
 9. የዩኒቨርሲቲው ካውንስል፣ የአስተዳደር ካውንስል እና የዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ ቃለ ጉባኤ ፀሐፊ በመሆን ይሠራል፣ አስፈላጊ ሲሆን ፕሬዚዳንቱ ወይም ፕሬዚዳንቱ የሚወክሉት በሚመሩት ስብሰባ ቃለ ጉባኤ ይይዛል፡፡
 10. የዩኒቨርሲቲው አጠቃላይ እንቅስቃሴን አስመልክቶ በየጊዜው ለበላይ አካል የሚዘጋጁ ሪፖርቶችን፣ መግለጫዎችን እና አስፈላጊ ሰነዶችን ያዘጋጃል፡፡
 11. በፕሬዚዳንቱ ሲታዘዝ የፕሬዚንቱን መልዕክት ያስፈጽማል፡፡
 12. በፕሬዚዳንት ጽ/ቤት የሚገኙ መረጃዎች በአግባቡ መያዛቸውን የሚስጢራዊ ሰነዶች በጥንቃቄ መቀመጣቸውን ይቆጣጠራል፡፡
 13. የቋሚ ሆነ ጊዜያዊ ኮሚቴዎችን የሥራ እንቅስቃሴ ይከታተላል፣ ድጋፍ ያደርጋል፣ ያስተባብራል፡፡
 14. በፕሬዝዳንቱና ም/ፕሬዝዳንቶች ሥር የሚገኙ የአስተዳደር ሰራተኞች የሥራ አፈጻጸምን ይከታተላል፤ይገመግማል፤ይቆጣጠራል፡፡
 15. ከፕሬዚዳንቱና ም/ፕሬዝዳንቶች የሚሰጡ ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራትን ያከናውናል፡፡

Contact

Dr. Haimanot Disassa Marru

 Acting as President of Assosa University

Telephone=+251-576-692-763

Fax=+251577750829

Email: This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

Ato Nigatu ambissa =Head of Presedant Office.

e-mail= This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

Telephone=+251577752036

Fax=+251577750829

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሥዕል አዉደ ርዕይ አካሄደ

ዩኒቨርሲቲዉ ከሰኔ 03-05/2009ዓ/ም በባንቡ ፓራዳይዝ ሆቴል ለ2ኛ ጊዜ ለእይታ ያቀረበዉ የሥዕል አዉደ ርዕይ የምረቃ በዓል ያደረገ ሲሆን ሥራዎቹ በፒካሶ የሥዕል አርት ክለብ በሰዓሊ ፋሲል ሙሉጌታ ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ፈጠራና ባህል ማዕከል ዳይረክቶሬት ጋር በመተባበር የተሠሩ መሆኑን መገንዘብ ተችለዋል፡፡

የተሰሩት ሥዕሎች በከፊል
አዉደ ርዕዩን የከፈቱት የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሀይማኖት ዲሳሳ እንዳሉት ዩኒቨርሲቲዉ እንደዚህ አይነት ልዩ ችሎታ ያላቸዉን ተማሪዎች ማጠናከርና እዉቅና መስጠት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዉ ወደ ፊትም ዩኒቨርሲቲዉ ከጎናቸዉ እንደሚቆም ቃል ገብተዋል፡፡ የተሠሩት የሥዕል ሥራዎቹም ጥሩና አበረታች መሆናቸዉን ጭምር ተናግረዋል፡፡

 

ሰዓሊዉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ ዓመት የመካኒካል ኢንጅነሪንግ ተማሪ ሲሆን ወደዚህ ሙያ የተቀላቀለዉ የ2ኛ ዓመት ተማሪ እያለ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ተማሪዉ እስካሁን ለዚህ ሥራ በግሉ ከ ብር 10,000 በላይ እንዳወጣና ለኪነ-ጥበቡ እድገት የዩኒቨርሲቲዉ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡ ይህንን አኩሪ ሥራ ራሱ ባቋቋመዉ ‘’ፒካሶ የሥዕል አርት ክለብ’’ ከሥሩ 750 አባላት በላይ በማሰለፍ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ተማሪዉ ጨምሮ ገልፀዋል፡፡ 

ተመልካቹ የሥዕል ሥራዎቹን ሲጎበኙ
አንዳንድ አስተያዬት ሰጪዎች በተማሪ ፋሲል ሙሉጌታ የተሰሩት የሥዕል ሥራዎችን አድንቀዉ ይበልጥ ለማጠናከር የዩኒቨርሲቲዉ ድጋፍ ወሳኝ መሁኑን ገልፀዉ ዩኒቨርሲቲዉ የአርት (ኪነ-ጥበብ) ትምህርት ቤት ቢከፈትላቸዉ ከዚህ የበለጠ መስራት እና ብዙ ተከታዮችን ማፍራት እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡

  

በአዉደ ርዕይዉ የተሳተፉት አስተያዬት ሲሰጡ